የመከላከያ ሰራዊት ቁልፍ እሴቶች

    

1. ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር

2. ምን ጊዜም የተሟላ ሰብዕና

3. ያልተሸራረፈ ዲሞክራቲክ አስተሳሰብና

4. በማንኛውም ግዳጅ/ሁኔታ የላቀ ውጤት ናቸው፡፡

1.ከራስ በፊት ለሀገርና ለህዝብ

-    ለህገ-መንግስቱ ታማኝ መሆንን: ለሀገርና ለህዝብ ህይወትን መስጠትን

-    በሠራዊቱና በሰርዓቱ እምነት መፍጠርን:ጀግንነትን:   ቁርጠኝነትን

-    ቀደምትነትን:ለሙያ ፍቅርና ክብርን መስጠት: ህግና ደንብን መከተል

-    ከራሱ በፊት ጓዱን ወይንም የሚመራውን ሰው ማክበርና ማሰብን

-    ስነ-ስርዓት ማክበርንና ራስን

2.ምንጊዜም የተሟላ ሰብዕና

-    የሞራል ጥንካሬን:   ከሙስና የፀዳና ሙሰናን የማይሸከም መሆን

-    የተስተካከለ ስነ-ምገባር መላበስን፣ ታማኝ መሆንን

-    ኃላፊነት የሚሰማው መሆንን/የባቤትነት ስሜት ያለው መሆንን:    ግልፅነትና  ተጠያቂነት

-    የራስንም ሆነ የሌላውን ክብር የማያንቋሽሽ መሆንን:  ሚስጥር መጠበቅን

 

3.ያልተሸራረፈ ዲሞክራቲክ አስተሳሰብ

-    በህዝብ ማመንን:የሰውን መብት ማክበርን:    በቡድን መስራትን

-    መግባባትንና መደጋገፍን: አሣታፊነትን:    የብሔር/ብሄረሰቦችን መብት ማክበር

-    የጾታና በሀይማኖት እኩልነት ማመንን: በዲሞክራሲ የተመረጡ የህዝብ ወኪሎችን ማክበር

-    ለብዙሃን ሃሣብ ተገዥ መሆንን:   ሃሣብን በግልፅ ማንሸራሽርን:  ዲሞክራሲያዊ ዝምድናን

4.በማንኛውም ግዳጅ/ሁሉም ሁኔታ የላቀ ውጤት

-    ቆጣቢነትን:ሳይንሳዊ አመለካከትን:  ከፍተኛ የሥራ ተነሳሽነትን

-    የፈጠራ ችሎታን: በጥራት ግልጋሎት መስጠትን:    የራስን ችሎታ ማሳደግ

-    ግዳጅን በጥራት መወጣትን:አርቆ ማሰብን: አርአያነትን

-    በቡድን መስራትን: ቀደምትነትን:ተጣጣፊነትን:   ወትሮ ዝግጅነትን

የካቲት 07/06/2005 ዓ.ም የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቀን


ህገ-መንግስታዊ ታማኝነታችንና ህዝባዊ ባህርያችን እንደተጠበቀ ይኖራል፡፡